Powered By Blogger

Thursday, October 11, 2018

Daniel Mulatu's Blog የዳንኤል ሙላቱ ጡመራ : ሚዘናዊነት  የት ገባያለፉትንክፍም ደግም ጊዚያት በሠላም አሳልፎ ለዚህ ቀን ...

Daniel Mulatu's Blog የዳንኤል ሙላቱ ጡመራ :
ሚዘናዊነት  የት ገባ
ያለፉትንክፍም ደግም ጊዚያት በሠላም አሳልፎ ለዚህ ቀን ...
: ሚዘናዊነት   የት ገባ ያለፉትን ክፍም ደግም ጊዚያት በሠላም አሳልፎ ለዚህ ቀን ያደረሰን አምላክ ክብርና ምስጋና ይግባው ፡፡ ሁላችንም እንደምናውቀው ሀገራችን ኢትዮጵያ የረጅም ጊዜ ታሪክ አላት የሚለው እውነ...

ሚዘናዊነት  የት ገባ

ያለፉትን ክፍም ደግም ጊዚያት በሠላም አሳልፎ ለዚህ ቀን ያደረሰን አምላክ ክብርና ምስጋና ይግባው ፡፡
ሁላችንም እንደምናውቀው ሀገራችን ኢትዮጵያ የረጅም ጊዜ ታሪክ አላት የሚለው እውነታ   ለድርድር የሚቀርብ አይደለም ፡፡ ችግሩ ግን የሀገራችን ታሪክ ምን ነበር ፣ መቸና የት ተፈጸመ፣ እነማን  ምን በጎና መጥፎ ነገር ሰርተው አለፉ ፣ ለምን ይህንን ሰሩ የሚለውንና በወቅቱ የነበረውን የውስጥና የውጭ  የፖለቲካ ጫና፣  የኢኮኖሚ እና የስልጣኔ   ገጽታ ፣ የሰዎች የአመለካከትና የእውቀት ጥልቀት፣ በጥቅሉ በማህበረሰቡ ዘንድ የነበሩ እሴቶች  ምን ነበሩ ብሎ በመረጃና በአስረጂ አባቶች ትንታኔ ላይ የተመሰረተ ምልከታ አድርጎ በማወቅና ባለማወቅ መካከል በሚመላለስ  የአመለካት ችግር ምክንያት የተፈጠረው የተወሰኑ ሰዎች የተሳሳተ ሀሳብ  መራገብ ነው ፡፡
በእኔ አምነት የአሁኑ ትውልድ በኢትዮጵያ የረጅም ጊዜ የታሪክ ጉዞ በአንድም በሌላ የራሳቸውን አሻራ ትተው ያለፉ ሁሉም ኢትዮጵያዊያንን ድርጊት፣ የእውቀት ጥልቀት፣ የስለምግባር ውበትና ጥንካሬ ፣ የእርስ በእርስ ክብር ፣ ለወገንና እና ለሀገር ያላቸውን ፍቅር፣ ቀና አመለካት፣ የታሪክ አሻራ በመጣል የማለፍ እሳቤ እና በጥቅሉ የተዋጣ ስብእና የመኮነን፣ የማሳነስና የመውቀስ የሞራል ብቃት አለው የሚል ሀሳብ የለኝም ፡፡ ብዙዎቹ አባቶቻችን ስለሀገራቸው  ክብርና ልእልና ሲሉ ቤተሰባቸውን፣ ቀያቸውንና ሀብት ንብረታቸውን  ትተው ህይወታቸውን ገብረዋል ፡፡ የዘር ፣ የጎሳ ፣ የቋንቋ ፣ የእውቀት ልዩነት ቦታ ሳይሰጡ እንደ አንድ ልብ አሳቢ እንደ አንድ አፍ ተናጋሪ በመሆን በጋራ በመተሳሰብ ኖረው ይህችን ታላቅ እና የተከበረች ሀገር ለእኛ  አውርሰው አልፈዋል ፡፡ ህዝብ  እንዲሰለጥን፣ ሀገር ተከብራና ተፈርታ እንድትኖር፣ አባቶች እንዲጦሩ፣ ልጆች በመልካም ስነ - ምግባር ታንጸው እንዲያድጉ እና የታሪክ ተወቃሽነት እንዳይመጣ የሁለንተናዊ እሳቤ ጭማቂ የሆነ አስተሳሰብን አንግበው የራሳቸውን ድርሻ በመወጣት ሀገርን አስረከቡ እንጂ እንደእኛ የራስን ጥቅም ብቻ በማስቀደም ተጨንቀው፣ በዘርና በጎሳ ላይ መሠረት ያደረገ የበቀል እርምጃ ሲወስዱ አልኖሩም፡፡ ልዩነት በእነሱ ጊዜ ቦታ አልነበረውም ፡፡ ቋንቋን፣ ባህልን በመወራረስ ፣ በጋብቻ በመተሳሰር እና በመተሳሰብ ወርቃማ ጊዚያትን አሳልፈዋል ፡፡
እነዚያ ብርቅየና ድንቅየ የጥንት አባቶቻችንና እናቶቻንን ለመውቀስ በቂ የሞራል ዝግጅት  ቢኖረንማ ኖሮ የሰሩትን ስራ እና ያለፈውን ታሪክ በሚገባ ተረድተን እና ካለፈው ተምረን ለሀገር ያለን ፍቅር፣ ለወገናች ያለን ክብር ከእነሱ በልጦ የሚታይበት መልካም እሴት በታየብን ነበር ፡፡ የአንዱን ቋንቋ ከሌላ ቋንቋ፣ የአንዱን ባህል ከሌላው ባህል ፣ የአንዱን ዘር ከሌላው ዘር  በማበላለጥና በመለያየት የልዩነት  መዝሙር ከመዘመርና በምንሰራበትና እውቀትን በምንገበይበት እድሜ ውስጥ እያለን በድንጋይ ውርወራና በሰልፍ ጊዜያችንን ባላጠፋን ነበር ፡፡ ቤተሰቦቻችንን ለመንከባከብ፣ ለመጦር፣ ለሁሉም ወገኖቻችን  ብድራቸውን ለመክፈልና በጥቅሉ ለወገናችንና ለሀገራችን የምናስብ ከሆነ ካለፈው በመማር የተሸለ ሰው ሆኖ መገኘት የእለት ከዕለት  ተግባራችንና የህይወት መርሃችን ሊሆን ይገባናል ፡፡
ኢትዮጵያ የሁሉም ብሔር ብሄረሰብ ሀገር ነች፡፡ ማንም ቀዳሚ ማንም ተከታይ የለም ፡፡ ማንም የበታች ማንም የበላይ የለም ፡፡ ሁሉም ሰው ክብር አለው ፡፡ በቋንቋ ፣ በዘር፣ በባህል እየለያዩ ማሸማቀቅና የበላይ የበታችነት ስሜት እንዲፈጠር ማድረግ ከእውቀት ማነስ፣ ከስነምግባር ብልሹነት፣ ከአመለካከት መዛነፍና በኢትዮጲያዊነት ካለማመን የመነጨ ህሳቤ እንጂ አንደተቆርቋሪ ሆኖ የሚያስቀርብ ሀሳብ አለመሆኑን መረዳት ይገባናል ፡፡
አመለካከታችን ሚዛናዊነትን መሠረት አድርጎ እና በእውቀት ላይ ተመስርቶ ካልተቃኘ ሃሳባችንና የምናደርገው ድርጊት ዘመን ተሸጋሪና ከታሪክ ተወቃሽነት የሚያድን ሊሆን አይችልም ፡፡ ለነገሩ  ይህች ሀገር በፈጣሪ ጥበቃ ስር ስላለች ነው እንጂ በየዘመኑ በሚነሱ አንዳንድ (የተወሰኑ  ) ሰዎች እሳቤና ድርጊት ቢሆን ኖሮ እንደሰዶምና ገሞራ በጠፋችም ነበር ፡፡ እና ሚዛናዊነት የት ገባ የሚያስብል እና ልዩነትን እያሰፋ በፍጥነት የሚጓዝ የወሬና የአሉባልታ እሳት እያቀጣጠልን የጥላቻና የራስ ወዳድነት  አመድን  በማቡነን እና  በሌሎች ዓይን ውስት እየጨመርን የተንሸዋረረ አመለካከትን አንፍጠር፡፡
ይቆየን !!
መስከረም 29/2011
አ/አበባ